ከቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡በመድረኩ በቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሥራ ገበያ ፍለላጎት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት አማካይነት የተጠና ጥናት ቀርቦ በግኝቶቹና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ላይ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ እንዲሁም በዘርፉ በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና አረጋግጦ እውቅና መስጠት የሚቻልባቸውን ጉዳዮችንም ተመልክተናል፡፡
በቀጣይም በሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም ሥራ እድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በቅንጅት ለመስራት ተግባብተናል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በቅንጅት ለመሥራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!