ቱ ማ ኢ ህዳር /2018 ዓ ም በተቋሙ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነር ሺፕ እና የህጻናት ቀን ከፍተኛ አመራሩና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል።የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት መንግስት ለኢንተርፕርነር በሰጠው ልዩ ትኩረት እንደሀገር በርካታ ኢንተርፕርነር መፈጠሩንና የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንዲሁም የህጻናት ቀንን አስመልክቶ እንደተቋም የህጻናት ማቆያ በመዘጋጀቱ ወላጆች ልጆቻቸውን በቅርበት እያዩ ሥራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ ማድረግ መቻሉን ፤ ለህጻናት ማሰብ ነገን ማሰተካከል እንደሆም ገልጸዋል ።
የተቋሙ ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በበኩላቸው በሀገር ደረጃ የኢንተርፕረነርሺፕ ቀንን አስመልክቶ እንደ ተቋም የሶስተኛ ዓመት ሰልጣኞች ላይ ሥራ ፈጠራ ላይ እየሰሩ ያሉ ሥራዎችን ገልጸዋል።
የኢንተርፕሪነር ቀንን በዘርፉ የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፍ ማቅረብ ፣ የፈጠራ ውድድሮች እና ልምድ ልውውጥ ለዘርፉ እድገት ምቹ መደላድል እንዲፈጠርና ስነ-ምህዳሩን በሁሉም ተቋማት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋም የሆነው የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት መሆኑን አቶ ይታሰብ ስዩም ተናግረዋል።
የኢንተርፕረነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማስፋት እና ችግሮችን በጥናት ለመፍታት እና ውጤታማ አሰራሮች ለመተግበር የፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ቤተሙከራ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡
የተቋሙ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ንግስት ሲሳይ ቀኑ ‘የህጻናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም ህጻናት ‘ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተናግረዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments