ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ መጋቢት 27 / 2011 ዓ.ም
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በደቦ፣ኬክና ጣፋጭ ምግቦች ዝግጅት በደረጃ ሶስት በማታ መርሀግብር ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀቁ፡፡
በኢንስቲትዩቱ የምግብና መጠጥ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወርቁ እንደገለጹት ሰልጣኞቹ በሙያ መስኩ አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን ገልጸውን በእለቱ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ካጠናቀቁት መካከል ሰልጣኝ ሰላማዊት ቱሉ እንደገለጸችው በሰለጠኑበት የሙያ መስክ በቂ እውቀትና ክህሎትን እንዳገኙና ወደ እንዱስትሪውም ሲቀላቀሉ ተወዳዳሪ ሆኖ የተሻለውን ስራ መስራት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የደቦና ኬክ ዝግጅት አሰልጣኝ ለሆኑት ለመምህር ዳንኤል መንግስቱ ከሰልጣኞቹ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

Recent Comments