ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ሰኔ 04/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል አሁን ካለው የቱሪዝም እድገት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን በአደረጃጀት፣በአሰራርና በሰው ሀይል የነበሩበትን ችግሮች በጥናት ለይቶ ከሰራተኞችና መምህራን ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በጥናቱ በተለየው መሰረት ተቋሙ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የሚገኘውን የቱሪዝም ዘርፍ በሚመጥን መልኩ አዳዲስ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት፣ መዋቅሩን በማሻሻልና የሰው ሀይልን በማብቃት ተወዳዳሪ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል::የአስተዳደር ዲን አቶ ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ጥናቱ የተቋሙን የውስጥ ችግሮችን ያሳየ በመሆኑ የተለዩ ችግሮችን በቅደም ተከተል ለማስተካከል ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በተለይም የማዕከሉ የደምብ ማሻሸያ እስኪጸድቅ ድረስ የውስጥ መዋቅርን በማስተካከል የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችም እየተሰራ ባለው ጥናት ላይ ያላቸውን ማስተካከያ በማከል ማዕከሉ በተሻለ መልኩ የተሰጡትን የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና ማማከር ተልዕኮ እንዲወጣ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡