ቱ .ማ. ኢ ሰኔ 1/2016 ዓ ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሆቴሎችና ቱሪዝም ድርጅቶች ጋር በትብብር የሰራቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀረበ።

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት የትብብር ስልጠናው ተቋሙን ፣ኢንዱስትሪውን እና ሰልጣኙን የሚጠቅም ሆኖ በድምሩ ለሀገር በሙያው የሰለጠነ ዜጋን ለማፍራት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል ። ቱሪዝም ከኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ እንደመሆኑ ከማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱና ከባለድርሻ አካላት ትብብር በዘርፉ የሰለጠ የሰው ሀይል በሰፊው ይፈልጋል።
ይህን ታሳቢ በማድረግ ይህ የትብብር ስልጠና ከመጀመሩ በፊት አብረን አቅደን ስለጀመርን አብረን ሪፖርቱንም መስማትና የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማሰቀጠል ከሁሉም አካላት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት እንዲያመች ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የሆቴል ባለቤቶች ማህበራት፣ሸፎች፣ የሆቴል ሥራአስኪያጆች የአስጎብኚ ድርጅቶች በዚህ ትብብር ስልጠና የተሳተፉ አሰልጣኞች ተገኝተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/