ታህሳስ 1/2018ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል ዲን በአቶ ዳዊት ሃይለ ሚካኤል ለምቶ ወደ ሥራ የገባውን ፖርታል ለፕሮሰስ ካውንስል አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎታል፡፡ አቶ ዳዊት እንደገለጹት ፖርታሉ የዘርፉን እቅድ፣ ሪፖርት፣ አርካይቭ፣ እና መስል ነገሮችን ያካተተ ሲሆን እቅድን ከ KPI አንጻር ግለሰቦች እና
እና ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ እና የቀራቸውን ተግባር እየለየ የሚያስቀምጥ ለአጠቃቀምም ቀላል ነው ብለዋል፡፡
የዘርፉ ሃላፊ፣ ዲኖች፣ ዴስኮች እና ባለሙያዎች በየራሳቸው ስም እና የይለፍ ቃል ሥራቸውን በሰነድ እና በፎቶ አስደግፈው ካስገቡ በኋላ በበላይ አለቃ እንዲፀድቅ በማድረግ ድምር ውጤቱን እየተነተነ አና ቀሪ ሥራዎችን እየለየ የሚያስቀምጥ ነው ተብሏል፡፡
የጥናት እና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ስለጥናት ውጤቱ ሲናገሩ ይህ ፖርታል ሀገራችን ካስቀመጠችው የዲደጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ማስፈፀም አንጻር አስተዋጽኦው ከፍተኛ ሲሆን እንደ ተቋምም የ ISO: 21001፡2025 ዲጂታል የማድረግ ዕቅድ አካል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በማጠቃለያም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ‘’የፕሮግራሚንግ ሥራ በጣም አድካሚ ነው፤ አቶ ዳዊት ለሰራው ሥራ ሊመሰገን ይገባል ካሉ በኋላ የለማው ፖርታል ከእቅድ ክፍል ጋር ተሳስሮ ተቋማዊ አሰራርን ድጂታል የማድረግ አካል እንዲሆን የሚመለከታቸው ክፍሎች አብረው እንዲሰሩ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
ፖርታሉን ያለሙት አቶ ዳዊት ሃይለ ሚካኤልን ከዚህ ቀደም የሰሯቸውን ቴክኖሎጂ ነክ የፈጠራ ሥራዎች ማስተዋወቃችን ይታወሳል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments