ብሉ ናይል ሃይኪንግ ከሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ደብረ ሊባኖስ ጉብኝት ፕሮግራም
የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን በማበረታታት የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት ዓላማ በማድረግ የተለያዩ የጉብኝት መርሐ ግብሮችን እያዘጋጀ መሆኑን የብሉ ናይል ሀይኪንግ መስራች አቶ ዘርሁን አለማየሁ ገለጹ።
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ነሐሴ 08/2013 ዓ.ም
ብሉ ናይል ሀይኪንግ በቱሪዝም ዘርፍ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ጎብኝዎችን መሰረት ያደረገ ጉዞዎችን እያዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ድርጅቱ ነሐሴ 08/2013 ዓ.ም ከሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር በመተባበር በደብረሊባኖስ አካባቢ ማህበረሰብ ተኮር ጉብኝት አድርጓል።
እንደዚህ አይነት ጉዞዎችን ማድረግ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማበረታታትና ማህበረሰቡ እርስበዕርስ እንዲተዋወቁ ለማድረግ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስተባባሪው አቶ ዘርይሁን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ጠቃሚ የሆኑ ቁሳቁሶች በተለይም የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ልገሳ አድርገዋል።
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በበኩላቸው የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።
Recent Comments