ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ የካቲት 19/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማስልጠኛ ማዕከል ለተቋማዊ ለውጥ የሚያገለግል ሪፎርም ሥራ በተቋሙ ከፍተኛ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ባላቸው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ተቋሙ አሁን ካለበት ደረጃ እንዲያድግና ለውጥ እንዲያመጣ የሪፎርም ሰነድ ማዘጋጀቱ ወሳኝ በመሆኑ ከተቋሙ በተወከሉ ቡድኖች እየተሰራ ያለውን ሥራ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በቦታው ተገኝተው በጎበኙበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ለስራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ ወደ ስራ እንደገቡና ተቋሙ ከአሥር ዓመት በፊት የነበረበትን የተለያዩ ሰነዶች በማንበብ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት መረጃዎችን በማሰባሰብ አሁን ያለበትን ደረጃ በመለየት ሰነዱን እያዘጋጁ እንደሆነ የቡድኑ ሰብሳቢ ዶ/ር ገብረኪዳን ፍስሃ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሰነድ ተዘጋጅቶ ሲያልቅ ተቋሙ አሁን ያለበትን ደረጃ ለማሳደግም ሆነ ለመለወጥ ወሳኝ እንደሆነ ዶ/ር ገ/ኪዳን ገልጸዋል፡፡
Recent Comments