ኢንስቲትዩቱ ቱሪዝምና ሰላም/Tourism and Peace/
በሚል መሪ ቃል የዓለም ቱሪዝም ቀንን እያከበረ ይገኛል።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የዓለም ቱሪዝም ቀንን አስመልክቶ ቱሪዝምና ሰላም በሚል መሪ ቃል በካፒታል ሆቴል በፓናል ውይይት ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት እያከበረ ይገኛል።
የፓናል ውይይቱን የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት ቱሪዝም ማህበረሰብን በማሰባሰብ በህዝቦች መካከል የባህልና የኢኮኖሚ ትስስር እንዲጠናከር ለማድረግ ቱሪዝምና ሰላም ያላቸው ቁርኝት ከፍተኛ ነው ብለዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም መንግስት በሚከተለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም መካከል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ይሆናሉ ተብሎ ከተመረጡት አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል ቱሪዝም ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ይህን ሀገራዊ ሪፎርም ተግባራዊ ለማድረግ የሀገራችን ሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በዘርፉ ብቃት ያለውን የሰው ሀይል በማፍራት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው የቱሪዝም አንቀሳቃሽ ሰላም ነው፣ ቱሪዝምም ሰላምን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ አለው፣ የሁለቱ የማይለያዩ ጉዳዮች ስለሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ለሚገኘው የቱሪዝም ቀን የተዘጋጀው መሪቃል ወቅታዊ ነው ብለዋል፡፡
የዓለም ቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ45ኛ በሀገራችን ለ37ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በሀገር ደረጃ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ቱሪዝምና ሰላም በሚል ርዕስ በመምህር ሳህሌ ተክሌ ጥናት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
#TourismDay #TTI #Tourism and #peace

Recent Comments