ቱ.ማ.ኢ ህዳር 20/2018 ዓ ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በትብብር ስልጠና በጋራ እየሰሩ ለሚገኙ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች በመደመር መንግሥት ስለቱሪዝም የተገለጸውን ክፍል ከኢዱስትሪ ጋር በማገናኘት መረጃ አቅርበዋል። በመደመር መንግስት ቱሪዝም ሀገርን የመግለጽ መድረክ ነው ብለዋል። በለውጡ መንግስት ቱሪዝም የኢኮኖሚ ምሶሶ ሆኖ ተዋቅሯል፤
ለምን የኢኮኖሚ ዘርፍ ሆነ ለሚለው አቶ ይታሰብ በመጽሐፉ የተጠቀሰውን ሲያብራሩ አንደኛ ቱሪዝም ያልተነካ እና ተዝቆ የማያልቅ ሀብት አለን፤ ስለዚህ ያለንን ሰፊ ሀብት አቧራውን እየጠረግን መስራትና ማሳየት ጀምረናል ብለዋል።
ሁለተኛ ቱሪዝም የውጪ ምንዛሪ በቀጥታ የምናገኝበት ፈጣን መንገድ በመሆኑ፤ ሶስተኛ የሥራ እድል በመፍጠር የሚስተካክለው የለም፤ በተለይ ለሴቶችና ለወጣቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ እድል ይፈጥራል።
በመጨረሻም የተጠቀሰው ሀገራዊ አንድነትና መግባባት ለማምጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው በተለይ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑን የገበታ ለሀገር፣ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ለዚህ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments