ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከጂንካ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ብዝሀነትና ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ለሥራ ዕድል ፈጠራ በሚል መሪ ቃል 11ኛውን የጥናትና ምርምር ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የጂንካ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሾ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ዩንቨርሲቲው በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኝ የብዝሃ ባህልና የብዝሃ ህይወት ስብስብ ያለበት፣ የአየር ንብረቱና የተፈጥሮ አቀማመጡ ጭምር ለቱሪዝም ምቹ የሆነ የ16 ብሄረሰቦች ስብስብ ያለበት መሆኑን ጠቁመው ይህ እንደ ሃገር በቱሪዝም ዘርፉ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ጋር ይህን መሰል የጥናትና ምርምር ጉባኤ ማካሄዱ በቱሪዝም ዘርፍ ዘለቄታዊነት ያለው ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የጥናትና ምርምር ጉባኤውን የከፈቱት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት ተልኮዎች አንዱ ምርምር እንደሆነ በዚህ የምርምር ጉባኤ የብዝሃ ባህል ስብስብ የሆነውና ከሀገራችን የቱሪስት መዳረሻ መስመሮች አንዱ የደቡብ ኦሞ ዞን በመሆኑ ከዩንቨርሲቲው ጋር በጋራ በመሆን በቱሪዝም ዘርፉ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላትና መሰራት የሚገባቸውን ደግሞ ትኩረት ሰጥቶ ለማከናወን ይረዳል ፤ ክህሎት ያለው በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥልጠና መስጠት እንዲቻል በጋራ ቢሰራ ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለዋል፡፡
በምርምር ጉባኤው አራት በቱሪዝም ዙሪያ የተደረጉ የጥናት ጽሁፎች ይቀርባሉ፡፡
ፕሮግራሙ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል፡፡