ቱ. ማ. ኢ ግንቦት 13/2017 ዓ. ምማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ አብሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ይህ የመግባቢያ ስምምነት ሁለቱ ተቋማት በጋራ እና በተናጠል የሚሰሩ ተግባራትን በመለየት እንዲሁም ምን፣ መቼ፣ ማን ይሰራል የሚሉትን ተጨማሪ እቅዶች በማዘጋጀት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡በተለይም ኢንስቲትዩቱ የፌደራል ተቋም እንደመሆኑ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠናን ክልሎች እንዲሰጡ ቢያደርግ ተደራሽነቱ ይጨምራል፤ የዜጎችን እንግልት እና እዚህ ያለውን ጫናም ይቀንሳል ብለዋል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በበኩላቸው በቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ የሚሰጡ ስልጠናዎችን በማዘመን ክልሎች እንዲያሰለጥኑ ማስቻል እንደሀገር ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመው፤ ስምምነቱ በስልጠና፣ በምርምርና ማማከር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዲን አቶ ግዛቸው በጋንፀ እንደተናገሩት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከሀምሳ ዓመት በላይ በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ልምድ ያካበተ በመሆኑ አብረን መስራታችን ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ጠቅሰው በቀጣይ በስልጠና በምርምርና ማማከር አብረን እንሰራለን ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et