ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 04/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና ኩሪፍቱ ሪዞርት በስልጠና፣ በሀገር በቀል የባህል ምግቦች ዝግጅት እውቀትን ለማስፋት፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች ጉዳዮች አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምክክር አድርጓል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናት፣ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በሀገራችን መስተንግዶ ኢንዱስትሪ ውስጥ የበኩሉን አሻራ እያሳረፈ ከሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር የሀገራችንን መስተንግዶ ባህል ደረጃ ለማዘጋጀት አብሮ ለመስራት ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በምርምር ሥራው በተለይ ባለፉት ዓመታት ሀገር በቀል የባህል ምግቦች ወደገበታ እንዲወጡ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል ምክክር መደረጉን አቶ ይታሰብ ገልጸዋል፡፡
ኩሪፍቱ ሪዞርትም የኢንስቲትዩቱን ሰልጣኞች በትብብር ስልጠና በመደገፍ የሥራ እድል እንዲያገኙ በማድረግ እንደሚቻል የሪዞርቱ ሥራ አስኪያጅ ገልጸዋል፡፡
የሪዞርቱ ማኔጅመንት አባላት በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚገኙ የተግባር ስልጠና ዎርክሾችና የማስተማሪያ ክፍሎችን ጎብኝቷዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et