ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ክህሎት ላይ ያተኮረ የተግባር ስልጠና ተቋም በመሆኑ በዘርፉ ለሚሰለጥኑ ባለሙያዎች የተሻለ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ከሀገሪቱ የተውጣጡ የቱሪዝም ምህራንእና የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ።
በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ ያለውን የረጅም ጊዜ ልምድ በመጠቀም በመስኩ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኞችና ባለሙያዎች ሙያዊ ልምድ የሚያካፍሉ ብቁ ምሁራን ያሉበት ተቋም ነው፡፡ በመሆኑ በዘርፉ የልህቀት ማዕከል በመሆን በየክልሉ ያሉ ተቋማትን ማብቃት ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገልጿል፡፡
ተሳታፊዎቹ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችም በሙያቸው ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማፍራት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፤ መንግስት ለባለሀብቶች የሚያደርገው ማበረታቻ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ታሳቢ አድርጎ መሆኑንም ጭምር በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቱሪዝምና በሆስፒታሊቲ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንዲሰራ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የውጭ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡
Recent Comments