መጋቢት 5/2015ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለቤት ውስጥ ሥራ ለሚሄዱ ሰራተኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
ስልጠናውን አስመልክቶ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ከኢፌዲሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ባደረገው
ስምምነት መሰረት የቤት ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ ካለው ፍላጎት የተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች በቂ የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ታስቦ ለ21 ቀን የሚቆይ የቤት አያያዝና እንክብካቤ የምግብ ዝግጅት እንዲሁም መሰረታዊ የቋንቋ ሥልጠና እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም አካላዊና ስነልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ በሚሄዱበት ቦታ በጥሩ ስነምግባር አገራቸውን የሚያስጠሩ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአረብ አገራት ለሥራ ሄደው የነበሩ እና የስልጠናው ተካፋዮች የነበራቸውን ተሞክሮ አካፍለዋል፡፡

Recent Comments