ቱ ማ ኢ የካቲት 28/2017 ዓ ምፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’በሚል መሪ ቃል ተከብሯል። በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት የሴቶችን ቀን በአንድ ቀን በማክበር ብቻ የሚታወስ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ኢኮኖሚያዊ፣
ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎን እና ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩታችን የቱሪዝም ማሰልጠኛ እንደመሆኑ በሆቴልና በቱሪዝም የሙያ መስኮች ሴቶች የበለጠ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበት እንደሆነ ገልጸው ሴቶች በተለያዩ ገቢ በሚያስገኙ አጫጭር ስልጠናዎች እንዲሳተፉ በማድረግና ሥራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የተቋሙ ሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ንግስት ሲሳይ እንደገለፁት ተቋሙ ሴቶችን በሥራ ቦታ ጠንካራ እንዲሆኑ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሰጠና የህጻናት ማቆያ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ማድረጋቸውን አመስግነዋል።
ለዚህ ፕሮግራም ልምዳቸውን ያካፈሉት የፓን አፍሪካንዝም ኒው ሆራይዘን መስራችና ዋና ጸሀፊ ወ/ሮ ህይወት አዳነ እንደገለጹት ሀገር በሴቶች ነፍስ ውስጥ ነች!! ነፍሷ ጠንካራና መልካም የሆነች ሴት ሀገርን ታሳርፋለች በማለት ከኢትዮጵያ በመነሳት አፍሪካ በመኪና በመዞር ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ ይከበራል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments