22/2015 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የቴክኒክና የሙያ ተቋማት የስልጠና ጥራትን አስጠብቀው እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገኙ በአገሪቱ ካሉ የቴክኒክና የሙያ ተቋማት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አንዱ ሆኖ ተመርጧል፡፡
ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ የጥራት አስተዳደር ስርዓትን /QMS/ን ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና በኢትዮዽያ የደረጃዎች ኢንስቲቲዩት የደረጃ ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር መሠረት በቀለ ናቸው፡፡
Recent Comments