ቱ.ማ.ኢጥር 26/2015ዓ.ም ኢንስቲትዩቱ በበጀት ዓመቱ ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን የአበይት ተግባራትን ጥንካሬና ክፍተት ለይቶ የ6ወር ዕቅድ አፈፃጸም አቀርቧል።

በመደበኛው ፣ በማታ እና ቅዳሜና እሁድ ከነባር ሰልጣኞች ውጪ የአዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ በዕቅዱ መሠረት አለመከናወኑ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመዘግየቱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
በጥናትና ምርምር እና ማማከር ዘርፍ በአዳዲሶቹ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ኮይሻ ፣ጎርጎራና ወንጪ ፕሮጀክቶች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያላቸው አስተዋጽኦ የተዳሰሰበት ፤ በኢንደስትሪው ተሰማርተው ላሉ ለባለኮከብ ሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት መስጠቱ ፣ በአጫጭር ሥልጠና እና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ከዕቅድ በላይ የተከናወኑ ሥራዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ለተቋሙ ሰራተኞች የኢንተር ፕርነርሺፕ ስልጠና እና የማነቃቂያ ስልጠና መሰጠቱ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከተከናወኑ አበይት ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህ ባሻገር ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች በጥንካሬ የሚታዩ መሆኑ ሪፖርቱ አመላክቷል።
የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው በመቀጠል በክፍተት የለያቸው የግዢ መጓተት አንዱ ሲሆን ለዚህም በኤሌክትሮኒክስ ግዢ የመንግስት ማዕቀፍ ውስጥ አቅራቢዎች ተወዳዳሪ ሆነው አለመገኘታቸው እንደ ችግር ተጠቅሷል።
በሌላም በኩል የተቋሙ ደንብ አለመጽደቁ ለሰው ኃይል ስምሪት እንቅፋት መሆኑ ተጠቅሷል።
በማጠቃለያው የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ካቀዳቸው ዓበይት ተግባራት ጥሩ አፈፃፀም ያላቸውን ማስቀጠል የደከምንባቸውን ደግሞ አጠናክሮና ተናቦ በመስራት ተቋሙ ሊያከናውናቸው የያዛቸውን እንደ (አይ ኤስ ኦ) ISO 2001:2015 የጥራት ደረጃ ለማስጠበቅ መስራት ፣ አዳዲስ ሰልጣኞችን በቀንና በማታው መርሃ ግብር መቀበል፣ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጸዋል።
የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ በአቶ ሀይሉ ነግዎ የዕቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክተር ቀርቧል።