የሰልጣኞች የሥራ ስነምግባርና ክህሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው ሰልጣኞች በተቋም ውስጥና በስራ ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ክህሎትና አመለካከት መሰረታዊ ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳል ያሉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በክፍል ውስጥ የሚሰጡ ምዘናዎችን ከማለፍ በዘለለ በዘርፉ ውስጥ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ አሰራሮችና እና የሥራ እድልን ለመፈጠር በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል። የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ እንደዚህ አይነት የፕሮጀክት ሃሳብ ላላቸው ሰልጣኞች ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ያላቸው ልምድ ለሰልጣኞች ያካፈሉት የሲምባ ቱር ባለቤትና የዓለም አቀፍ ጉዞ አማካሪ አቶ የውብሸት አለማየሁ ስኬታማ ለመሆን የመጀመሪያው ዓላማ ሊኖራችሁ እና ለሥራው የሚያስፈልግ ክህሎትና የሙያ ፣ስነምግባር መያዝ ይጠበቅባችዋል ብለዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ሰልጣኞች በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚኖራቸው ክህሎትና አመለካከት ላይ ግንዛቤ የሚያሳድግ ስልጠና መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ ገልጸዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቴክኖሎጂ በኢንስትራክተር ቲጃኒ ሁሴን፣ አስተሳሰብና የስነምግባር ዕድገት በኢንስትራክተር ሰለሞን አሰፋ እና የኢንዱስትሪ ግንዛቤ በኢንስትራክተር ታደሰ ሞላ ተሰጥቷል፡፡
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication