የኢንቲትዩቱ ሠራተኞች ውይይት አካሄዱ

የቱሪዝም ማልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች “የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ እንደሀገር የተሰሩ ሥራዎች እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
የውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በተለይ ከአምስት ዓመት ወዲህ በሀገራችን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ሀገራችን በአፍሪካ አህጉረ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች ሀገር ናት ብለዋል። ሀገርን እየመራ ያለው የብልጽግና መንግስት በነበሩ ፈተናዎች ያልተንበረከከ ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ጥበብና ልምድን እያካበተ የመጣ በመሆኑ ታሪካዊት፣ ቀደምትና ስመ ገናና የሆነችውን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ለማሻገር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ይህን ለማሳካት ሁሉም የበኩሉን ርብርብና ድጋፍ በማጠናከር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ እድገት በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደ ሀገር የህዝቦች ትብብር፣ የዜጎች ክብር፣ ሀገራዊ ልዕልና እና ሰብዓዊ ብልጽግና ያለባት ሀገር እንዲኖረን የጋራ ህልም ሊኖረን ይገባል ብለዋል።
ሰነዱን መነሻ በማድረግ ከሰላም ጉዳይ፣ የኢኮኖሚ እድገት ከተሳታፊዎች እንደተቋም ወደፊት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/