በሪፎርም ሥራዎች ከዝግጅት ምዕራፍ ወደ ተግባር ምዕራፍ ይፋዊ የሽግግር መርሃ ግብር ተካሄደ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የመንግስት አስተዳደር የሪፎርም ሥራዎች ዝግጅት ምዕራፍ ማለፉንና የተግባር ምዕራፍ ጅማሮን አስመልክቶ የእቅድ ውይይትና ለኮሚቴ አባላት የእውቅና መርሃ ግብር ተከናውኗል። እቅዱን የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት አቅርበዋል።

አቶ ሀብታሙ እቅዱ ሁሉንም የሥራ ክፍሎች ወደ ተግባር የሚያሸጋግርና ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስችል እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።በማጠቃለያው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በሪፎርም እና በISO 21001:2018 የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የኮሚቴ አባላት ተቋሙን ያኮሩ መሆናቸውን ገልጸው በዝግጅት ምዕራፍ ያሳያችሁትን ትብብር በተግባር ምዕራፍ እንድትደግሙትና ላለፈውም ለማማሰገን ነው የተገናኘነው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የ ISO21001:2918 እውቅና ማግኘቱ ይታወሳል።
ትክክለኛ ጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/