ኢንስቲትዩቱ ከኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚሰሩ ዕቅዶች ላይ ምክክር አካሄደ።
በምክክር መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው እንዲዘምን፤ አገልግሎቱም ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲሻሻል እና ለወጣቶች ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር እንዲቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ዘርፉ የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማቅረብ፣ የጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ በተለይም ሀገር በቀል የምግብ ዝግጅት እውቀቶችን ለማስተዋወቅና እንደ ሀገር ተጠቃሚ ለመሆን እንዲቻል እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ም/ዋና ዳይረክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም የተሰራው የኢንዱስትሪ ስልጠና ፕሮግራሞች ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አሁን በዘርፉ እየተሰጠ ካለው የስልጠናው ደረጃ ከፍ ባለ በደረጃ ማስተማር የሚያስፈልግ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ከተገኙት ተሳታፊዎች መካከል አቶ ቴዎድሮስ ሳህለ በሀገር በቀል የምግብ ዝግጅቶች የሀገራቸውን ቱሪዝም ያሳደጉ ሀገሮች መኖራቸውን ገልጸው በሀገራችን ገና ያልተሰራበት የቱሪዝም ሀብት በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸውን ሥራዎች መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የኢንዱስትሪ ስልጠና ፕሮግራሞች ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በኢንስትራክተር ሳህለ ተክሌ፣ አገር በቀል የምግብ ዝግጅት አውቀት ጥናት በኢንስትራክተር ሀብቱ ተካ፣ የተቋሙ ተመራቂ ሰልጣኞች የሥራ እድል ፈጠራን የሚመለከት ጥናት በኢንስትራክተር አለምነህ መርሻ እና የተቋሙ 2016 በጀት ዓመት እቅድ በአቶ ተመስገን በቀለ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication

Recent Comments