ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎች አቀባበል አደረገ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም አዳዲሰ ሰልጣኞች አቀባበል አደረገ።
በአቀባበሉ ፕሮግራም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያቀረቡት የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደተናገሩት ወደዚህ አንጋፋ ተቋም በመቀላቀላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ተቋሙ ከሌሎች ተቋማት ለየት የሚያደርገው በተግባር የተደገፈ እና በተለያዩ ሶፍትዌር የታገዙ ቤተሙከራዎች ስልጠና መስጠቱ መሆኑን ገልጸው እንዲሁም በዘርፉ ብቃት ያላቸው አሰልጣኞች መኖራቸው እንደሆነ ገልፀው ፤ከሰልጣኞች የሚፈልገው ለኢንደስትሪው የሚመጥን ስነምግባር መላበስ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የተቋሙ ቮኬሽናልና ጋይዳንስ እና የትብብር ስልጠና አሰተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ ስለትብብር ስልጠና ግንዛቤ ሰጥተዋል።
የሬጅስትራርና አልሙኒም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ወልዴ፣ የሆቴል ፋካልቲ ዲን አቶ ዮናስ ቶሎሳ ፣ የቱሪዝም ፋካሊት ዲን ተወካይ አቶ ማሩ እማኙ እንዲሁም የተቋሙ ስነምግባር ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ወ/ሪት ዓለምፀሐይ በቀለ ጨምሮ በስልጠና ወቅት እንደ ዲፓርትመንት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሰፊ ግንዛቤ በመስጠት ሰልጣኞችም ያልተረዱትን በመጠየቅ ወይይት ተደርጎበታል።
ISO21001 2018 በተመለከተ የተቋሙ ኳሊቲ አሹራንስ ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር አስቻለው አደራ ግንዛቤ ተሰጥቷል ።