የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 20ኛውን የጸረ ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገለው” በሚል መሪ ቃል አከበሩ።

ዕለቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አሰግድ ጌታቸው ህዝብና መንግስት የሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት የሀገራችንን ዕድገት ከሚገቱ ተግባራት የጸዳ አሰራር እንዲኖር የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለዋል።
በአከባበሩ ላይ የተገኙት የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እሼቴ አስፋው በበኩላቸው ሙስና የግለሰብ ጉዳይ ብቻ አይደለም በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን ላይ እንደ ካንሰር የሀገርን ልማት የሚጎትት በመሆኑ በጋራ መታገል የሚያስፈልግ መሆኑን ገልጸዋል።
አስፈላጊውን አደረጃጀትና ስልት ፈጥረው ሙስናን የታገሉ ሀገራት እድገታቸውን አረጋግጠዋል ያሉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እኛ ከድህነት ለመውጣት የምንጥረውን ያህል ሙስናን ካልታገልን ከድህነት መውጣት አንችልም ብለዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ ለግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ተሳታፊዎችም አስተያየት ተሰጥተዋል። ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication