ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በኮንታ ዞን ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመደገፍ በሚያከናውናቸው ተግባራት እንደሚያመሰግኑ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ፡፡

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ነጋ አበራ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከዞኑ ጋር በመተባበር በአካባቢው የሚገኘው የቱሪዝም ጸጋን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል ስልጠናዎችን በመስጠት እያደረገ ላለው ተግባር ምስጋና በማቅረብ በቀጣይነት በተጠናከረ ሁኔታ በቅንጅት አብሮ እንደሚሰራ ከኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
በዞኑ ውስጥ ከፍተኛ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሀብት መኖሩን የገለጹት አቶ ነጋ አበራ ይህን ለስራ ዕድል ፈጠራና ከዘርፉ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በቀጣይነት ከማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ጋር አብሮ ሊሰሩ የሚቻልባቸውን ጉዳዮች አብራርተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅም ግምባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በበኩላቸው በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማማከር አገልግሎቶች ከዞኑ ጋር የሚሰሩ ጉዳዮችን ገልጸው በቀጣይነት በቅንጅት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
የኮንታ ዞን ከፍተኛ የቱሪስት ሀብት የሆኑት እንደ ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ፣ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ እየለሙ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች፣ ቱባ ባህል ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች የሚገኙበት ነው፡፡
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።