ሶስተኛ ዓመት የቱሪዝም ተማሪዎች በመልካ ቁንጥሬና በጢያ ትክል ድንጋይ የተግባር ስልጠና አደረጉ፡፡

በመልካ ቁንጥሬ ታሪካዊ ቦታ ጥንታዊ የሰው ልጆች ለሥራ ይጠቀሙበት የነበረ በርካታ ከድንጋይ የተሰሩ መሳሪዎችና የእንስሳት ስብስብ የተገኙበት ቦታ እንደሆነና ቦታውም በ1965 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንደተጠና አስጎብኚው ገልጸዋል፡፡
የጥናቱ ውጤትም ሥፍራው ከስምንት መቶ ሺህ ዓመት በላይ የሰው ልጆች መኖሪያ ሆኖ ያገለግል እንደነበረ የሚያመለክት ሲሆን ሥፍራውን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው የሰው ልጆች በህይወት ሂደት ቀጥ ብለው ለመራመድ የጀመሩበት ፣ ድንጋይን ከድንጋይ በማጋጨት እሳትን የፈጠሩበት ፣ ቤተሰባዊ አኗኗርን የጀመሩበት ረዥም እድሜ የኖሩ የሰው ልጆች ቅሪተ አካል በመገኘቱ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
ሌላው ጢያ ትክል ድንጋይ ነው፡፡
* ጢያ ትክል ድንጋይ በ1972 ዓ ም በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል ።
* ትክል ድንጋዩ ትንሹ አንድ ሜትር ሲሆን ትልቁ አምስት ሜትር ነው።
* በድንጋይ ተቀርጸው የሚታዩት ምስሎች አምስት ናቸው ። እነሱም
1, ሳንጃ ምስል
2, የከበሮ ምስል
3, የሴት ምስል
4, የጋሻ ምስል እና
5, የወንድ ብልት ምስል መሆናቸውን የመስህቡ አስጎብኚ አቶ ሲሳይ ዋቅጅራ ገልጸዋል ።
በዚህ የተግባር ስልጠና የተሳተፉ ሰልጣኞች ለቀጣይ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለስራ ዕድል ፈጠራ እንዲያመቻቸው ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ የቱሪዝም መምህር አቢይ ንጉሤ ተናግረዋል፡፡ ይህ ስልጠና ቀጣይ ወደ ስራ ዓለም ሲገቡ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ጎብኚ ይዘው ሲመጡ ለማስተዋወቅ እንደሚጠቅማቸው የቡዱኑ ሰብሳቢ ተማሪ ሃሌሉያ ተመስገንም ተናግሯል፡፡