“የሠራተኛውን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀም ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆን እንሰራለን። “አቶ ገዛኸኝ አባተ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የህብረት ስራ ማህበር በማቋቋም በዘላቂነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለ ጉዳዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ሰራተኞች በህብረት ሥራ ማህበር በመደራጀት ያለውን የኑሮ ጫና ለመቋቋምና በዘላቂነት ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚያግዝ ገልጸው የሠራተኛውን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀም ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
የህብረት ሥራ ማህበር የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች የሚያቋቁሙት የንግድ ማህበር መሆኑን የገለጹት በህብረት ሥራ ኮሚሽን የህብረት ሥራ ማህበር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ድሪባ በቀለ በገበያ ውስጥ የመደራደር አቅምን የሚጨምርና በፍትሐዊነት ከግብይት ተጠቃሚ ለመሆን ያስችላል ብለዋል።
ከሰራተኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ከህብረት ሥራ ኮሚሽኑ ባለሙያ ምላሽና ማብራሪያ ሰሰጥቷል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።
Recent Comments