ኢንስቲትዩቱ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የዓለም ቱሪዝም ቀንን በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልላችን ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ሳይነካ የሚገኝበት፤ ሰውና ተፈጥሮ ተግባብቶ ለአዕምሮ ሰላምን የሚሰጥ አረንጓዴ አሻራ የሚገኝበት መሆኑን በመጠቆም ይህንን እምቅ ሀብት እንደሚፈለገው አልተጠቀምንም ሆኖም አሁን የተጀመሩ ሥራዎችን በማስቀጠል ከፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ብለዋል። ይህንን ፕሮግራም ላዘጋጁ ተቋማትና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ፕሮግራሙን አስመልክቶ የዘንድሮ የዓለም ቱሪዝም በዓለም 45ኛ በሀገራችን 35ኛ ጊዜ በሚከበረው ‘ቱሪዝም ለሰላም ‘ በሚል መሪ ቃል ነው። ይህንን ዝግጅት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እንድናከብር ክልሉ የቡና ፣ የልዩ መልክዓ ምድር እና የተፈጥሮ መስህብ፣ የማርና ቅመማቅመም መገኛ መሆኑና እምቅ የቱሪዝም ሀብት ያለበት አከባቢ በመሆኑ ለአከባቢውም ሆነ ለሀገር መነቃቃት በመፍጠር ለማስተዋወቅ ጭምር እንደሆነ ተገልጿል ።
በክልሉ ስለሚገኙ ቱሪዝም ዘርፍ ለስራ ዕድል ያለው ፋይዳ የተጠና ጥናታዊ ጹሁፍ በተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ አህደር ጠና አቀርቧል። ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ምን ያህል ጊዜ እንደሚያሳልፉና የጉዞ ፓኬጅ ሰነድ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አቢይ ንጉሴ አቅርበዋል።
በዚህ ፕሮግራም በክልል የሚገኙ ስድስት ዞኖችና ባህላዊ ምግቦችን በተመለከተ የተሰራ ሰነድ ያቀረበው የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መለሰ ወርቁ ወደ ኢንተርናሽናል ሆቴሎች ለማስገባት የማስተዋወቅ ሥራዎች ተሰርቶ ሰነድ ቀርቧል።
ሌላው ከቦንጋ ዩንቨርስቲ አቶ ሰለሞን በተመሳሳይ ቱሪዝምን ወደ ስራ እድል እንዴት መቀየር እንዳለበት የሚገልጽ ሰነድ አቅርቧል።
በቀረቡ ሰነዶች ውይይት ተደርጎበታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments