ኢንስቲትዩቱና EASTRIP ትብብር ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽንና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት (EASTRIP) በጋራ በመሆን ከአርባ አንድ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ለተገኙ የሆቴል እና የቱሪዝም መምህራን እየተሰጠ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል፡፡
በመዝጊያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ የትምህርትና ስልጠና ምክትል ዋና ዳይሬከተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በዘርፉ የሚታየውን ብቃት ያለው የሰው ሀይል እጥረት ለማሻሻል ኢንስቲትዩቱ ልብቻው የሚያፈራው የሰው ሀይል ሀገራችን ካላት የቱሪዝም ዘርፉ ስፋት ጋር ሲነጻጸር አናሳ ስለሆነ በዘርፉ ስልጠና እየሰጡ ካሉ ተቋማት ጋር ተቀራርቦ መስራት ይገባል ብሏል፡፡
ስልጠናው ለዘጠኝ ቀናት በምግብ ዝግጅት (culinary Art)፣ ኬክና ዳቦ ዝግጅትና ቱሪዝም ላይ ያተኮረ በተግባር የተደገፈ ስልጠና ተሰጥቷል።
ሰልጣኞችም ኢንዱስትሪው ምን አይነት የሰው ሀይል እንደሚፈልግ ለመለየትና የሚሰጡትን ስልጠና ለማሻሻል እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን ሲሰጡ ከነበሩ ከኢንዱስትሪው የተሳተፉ የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች መካከል ሼፍ ካብራክ ተኮላ በስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙያው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የለየንበት ነው ብለዋል።
በመጨረሻም ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
Recent Comments