የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት አሰጣጥን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች መተግበር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ፡፡
የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት አሰጣጥና አጠቃላይ የጉዞ እንዱስትሪውን በቀላሉ ማስተዋወቅ በሚፈለገው ጊዜ ውስጥ መረጃ መስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚገባ የሚመለከት ከተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተገኙ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንስትራክተር ዳዊት ኃ/ሚካኤል ሲሰጡ እንደገለጹት እየተፈጠሩ የሚገኙ ለቱሪዝም እንዱስትሪው አጋዥ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ቀላል እያደረጉ ነው ብለዋል።
በቴክኖሎጂን በመጠቀም የመዳረሻ ቦታዎችን በማስተዋወቅ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሀገራችን የዓለም ቅርስ የሆነው የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስትያናትን በቨርቹዋል ሪያሊቲ ለማስተዋወቅ የተሰራውን ሥራና በሆቴሎች ውስጥ ከአንድ ማዕከል በሲስተም የተያያዙ አገልግሎቶችን እንደምሳሌ ተጠቅሰዋል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።
Recent Comments