ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ስርዓት ISO21001/2018 ትግበራ ለመጀመር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ስርዓት ISO21001/2018 ትግበራን ከጥቅምት 01/2016 ዓ.ም ለመጀመር የመጀመሪያ ዙር ለሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የቱሪዝም አንዱስትሪው የሚፈልገውን ብቃት ያለውና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፍራትና የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ለመወጣት ሁሉም ሰራተኛ የታቀደውን ተግባር በቁርጠኘነት መፈጸም ይገባል ያሉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የጥራት ደረጃው ከጥቅምት 01/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን ከተካፈሉት መካከል ወ/ሮ ዝናሽ ብሩክ ስልጠናው ስራ ለመስራት ስለ ጥራት ደረጃውን ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የጥራት ደረጃውን ለመተገበር በቁርጠኝነት መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን አሰፋ ለጥራት ደረጃው ትግበራ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ አንለይ ሙልጌታ በቡኩላቸው የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና በመስጠት ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሀይል ማፍራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክ