የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የሰራተኞች ህብረት ሥራ ማህበር ተቋቋመ።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰራተኞች ህብረት ስራ ማህበር ተቋቋመ።
የህብረት ስራ ማህበሩን ለማቋቋም በተዘጋጀው የሰራተኞች ውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ይህ ህብረት ስራ ማህበር የሰራተኞችን ኑሮ ለመደጎምና በመደራጀት ጥቅሞች ለማግኘት እንደሚረዳ ገልጸዋል። ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተቋሙን ህብረት ስራ ለመደገፍ የመጡት ባለሙያዎች ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት አደራጅ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገነነ ታዬ መንግስት በአዋጅ በሰጠው ስልጣን መሰረት ህብረት ስራዎችን በክ/ከተማ በመመሪያው መሰረት እንደሚያቋቁሙ በመግለጽ የተቋሙ ህብረት ሥራ ማሟላት ያለባቸውን ሰነደች በማሟላቱ ከዛሬ ጀምሮ “ሰላም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ህብረት ሥራ ማህበር” መቋቋሙን አባላቱ በተገኙበት አብስረዋል።
ስለህብረት ስራ ማህበር መመሪያ መብትና ግዴታም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ሰባት ስራ አስፈጻሚዎች ፣ሦስት ቁጥጥር ኮሚቴና ሦስት ግዥ ኮሚቴዎችም ተመርጧል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/

Recent Comments