ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአይነቱ ልዩ በሆነው ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፕታሊቲ አውደርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ለሀምሳ አምስት ዓመታት በደረጃና በዲግሪ በተለያዩ የስልጠና መርሃ ግብሮች በሆቴልና ቱሪዝም የሙያ መስኮች እያሰለጠነ የቆየ፣ በዘርፉ ጥናቶችን በማካሄድና የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ለሀገራችን ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ተቋም ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ሀገራዊ ኃላፊነትና ትግባራትን ለመወጣት የሚያከናውናቸውን ስራዎች በኤግዝቢሽኑ ላይ እያቀረበ ይገኛል፡፡
አውደ-ርዕይውን የጎበኙት የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ዝግጅቱ አገራችን ያላትን የቱሪዝም ሃብቶች የሚያስተዋውቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አውደ ርዕው ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ስለተቋሙ መረጃዎችን ለማግኘትና በተለይም የሚሰጣቸውን ትምህርት አስመልክቶ በቂ መረጃ ለማግኘት ኤግዝህቢሽኑን እንዲጎበኙ ኢንስቲትዩቱ ይጋብዛል፡፡
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችንይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication