አቶ እስኪንድር ውብሸት የኢንስቲትዩቱ የቀድሞ ተማሪየቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቀድሞ ሰልጣኝ አቶ እስኪንድር ውብሸት ከ40 ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ትምህርት ቤታቸው ላደረገላቸው ውለታ በሆቴል ዘርፍ ተግባርን መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ሁለት መጽሐፍ ለኢንስቲቲዩቱ አስረክበዋል።

ስጦታውን የተረከቡት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተአቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለጹት ለተቋሙ ለሰጡት የመጽሐፍ ስጦታ ምስጋና አቅርበው ወደፊት በተግባር ስልጠናና ኢንስቲትዩቱን ከሌሎች ተቋማት ጋር በማገናኘት ድጋፋቸው እንዲቀጥል ሎሎችም የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኝ የነበሩ በዘርፉ ያካበቱትን እውቀት እና ተሞክሮ አሁን ላሉ ሰልጣኞች ልምድ እንዲያካፍሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስጦታውን የሰጡት አቶ እስክንድር ውብሸት በበኩላቸው በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ እንደ እ.ኤ.አ. 1981 በእንግዳ አቀባበል ተመርቀው ለሁለት ዓመታት በኢንስቲትዩቱ በአሰልጣኝነት ማገልገላቸውን እና ኢንስቲትዩቱ ያደረገልኝ ብዙ ነው” ያሉ ሲሆን አሁን ባላቸው ጊዜ ለተቋሙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et