ኢንስቲትዩቱ ያካሄዳቸውን ሀገራዊ ጥናቶች የመጀመሪያ በዘርፍ ደረጃ ገመገመ፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሆስፒታሊቲ ዘርፉን አገልግሎት ለማሻሻል የሚያስችሉ ሀገራዊ የሆኑ አምስት ጥናታዊ ጽሁፎች በጥናትና ምርምር በዘርፍ እንደተገመገሙ
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ገልጸዋል፡፡
በተለይ በዘርፉ ያለው የሰው ሀይል ፍላጎትን እና ከቴክኖሎጂ ሽግግር ጋር የተያያዙ ሁለት ጥናቶች የመጨረሻ ግምገማ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል።
አቶ ይታሰብ አክለውም የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት (Tracer Study), የባህል ምግቦች፣ ሀገር በቀል እውቀት ጥናት፣ የቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ትንተና ጥናት እና የሆስፕታሊቲ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ጥናቶች ተገምግመዋል ብለዋል፡፡
በተለይ በዘንድሮ ዓመት የባህላዊ ምግብና መጠጥ ዝግጅት በሃዲያ፣ ወላይታ፣ ኮንሶ፣ ዳውሮ፣ ወራቤ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተካሂዷል።
ይህን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት በሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦችን ሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታስቦ መሆኑን የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊው ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/