በጥናትና ምርምር እና የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል በጥናትና ምርምር እና የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡
ኢንስቲትዩቱ ባለው ሰው ሀይልና አደረጃጀት ሀገራዊ የሆኑ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተቋሙ አገልግሎቱን በሚገባ ተደራሽ ለማድረግ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ የሰራተኞችን አቅም መገንባት መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ
ተቋሙ በጥናትና ምርምር ስራዎች ረጅም ጊዜ የቆየ ልምድ ያለው ቢሆንም ይህን መሰል መድረክ መፈጠሩ የማሻሻያ ሃሳቦችን ለማመንጨት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመቅሰም እና በዘርፉ ህብረተሰቡን ለመደገፍ ያግዛል ብለዋል።
ስልጠናው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመጡ ዶክተር ደሜ አበራ እና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ዶክተር ጡሩዬ አለሙ በህይወት ክህሎት(life skill)፣ እራስን ማሻሻል(self development)፣ የጥናት ሥነ-ዘዴ(Research Methodology) አና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ተሰጥቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/