በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ ማጋራት ተደረገ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ሙስሊም ወገኖች የማዕድ ማጋራት አደረገ፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት በወረዳ 11 በርካታ የማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት እያከነወኑ መሆኑን በመጠቆም ይህ ማዕድ ማጋራት አብሮትን ለመግለጽ ታስቦ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ለ80 ቤተሰብ ከ160ሺ ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገልጿል፡፡