የ2016በጀት ዓመት ሀገራዊ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀረበ።

በቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት ዓመት ሀገራዊ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለኢንስቲቲዩቱ አጠቃላይ ሠራተኞች ቀረበ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የሀገራዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን አስመልክቶ እንደገለጹት በሀገራዊ አፈጻጸሙ እንደሀገር እና እንደ ሴክተር ምን ያህል አፈፃፀም እንዳለ ለመገምገም የሚረዳ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ እንደ ተቋም የድርሻችንን ለመውስድ ይረዳናል ብለዋል።
ሀገር አቀፍ አፈጻጸም ሪፖርቱ በማክሮ ኢኮኖሚ ፣በኢኮኖሚ ፣ በግብርና ፣ በመሰረተ ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው። በሪፖርቱ አንዳንድ ተቋማት ከዕቅድ አንፃር ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸው እንዳሉ ሪፖርቱ ያመላክታል።
ሀገራዊ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እያቀረቡ ነው።
ትክክለኛ የኢንስቲትቱን መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩቱን
ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ