የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጎበኙ።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች ከንድፈ ሃሳብና
ከተግባር ስልጠናዎች ባሻገር የሀገራችን የዲሞክራሲ ስርዓት ከሚገለጽባቸው ተቋማት አንዱ የሆነውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መጎብኘታቸው ጠንክሮ ለመማር ሞራል እንዳገኙበት ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉት የክፍል ተወካዮች መካከል የአብስራ ታደለ ያየነው ነገር ትልቅ ደስታ የፈጠረብን ፣ ያላየነውን ነገር እንድናይ፣ የማናቃቸውን ነገሮች እንድናውቅ፣ የሀገር ፍቅር እንዲሰማን እና ህልማችንን እውን ማድረግ እንድንችል፤ የራሳችንን ስነ ልቦና ከፍ ያረግንበት ጉብኝት ነው ብሏል፡፡
በተጨማሪም የተቋሙ አመራሮች ይህን ጉብኝት ማመቻቸታቸው ለሰልጣኙ ያላቸውን ትልቅ ቦታ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ 27 የሰልጣኝ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ የተቋሙ ከፍተኛ አሰልጣኝ አቶ ታደሰ ሞላ አስተባብረውታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments