ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ለአዲስ ህንጻ ግንባታ ውል ተፈራረመ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንሰቲትዩት በዓለም ባንክ EASTRIP ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባው አዲስ የስልጠናና አስተዳደር ቢሮ ህንጻ ግንባታ ከK2N ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅት ጋር ውል ፈረመ።
ይህ በዓለም ባንክ ፕሮጀክት ድጋፍ የሚደረግበትን ግንባታ በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት ውጤታማ እንዲሆን እና በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡ አማካሪ ድርጅቱ በፕሮጀክቱ ገንዘብ ድጋፍ አማካይነት የሚገነባውን አዲስ ህንጻ ከዲዛይን ሥራ ጀምሮ ኮንትራክተር የሚቀጠርበትን ሰነድ የማዘጋጀት ፣ ግንባታውን የመከታተል ተግባራትን የሚሰራ በመሆኑ በተባለው ጊዜ ውስጥ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አቶ ጌታቸው ነጋሽ አሳስበዋል፡፡
የK2N ኮንስትራክሽን አማካሪ ድርጅት አስተባባሪም በበኩላቸው ሁላችንም ሥራዎችን ተቀብለን እና ተከፋፍለን በተባለው ጊዜ ለመጨረስ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
የፊርማ ስነስርዓቱ በተቋሙ ማኔጀመንት አባላት እና የEASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪዎች በተገኙበት ተከናውኗል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments