የ2016 ዓ ም የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሪፖርት ለተቋሙ ሰራተኞች ቀርቦ ተገመገመ።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት በተቋሙ ባለሙያዎች እና አመራሮች የተሰሩ ሥራዎች ሪፖርት ሲቀርብ በበጀት ዓመቱ ከታቀደው ዕቅድ አንፃር በዘጠኝ ወራት የሠራነውን መገምገማችን ምን ያህል እንደቀረን ለማወቅ ፤ ባሉን ቀሪ ወራቶች ደግሞ ፈጥነን እና ፈጥረን ወደ ሥራ ለመግባት እና ጠንክረን የሰራናቸውን ሥራዎች በዛው ልክ ማስቀጠል እንድንችል ያግዘናል ብለዋል።
የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን የተቋሙ ዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳግም አዲሱ ያቀረቡ ሲሆን ከዚህ በፊት የተነሱና ምላሽ ያገኙ የመልካም አስተዳደር ጉዳዪችን በተመለከተ ለውጥ እና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ሰለሞን አሰፋ አቅርበዋል።
የዘንድሮው የሥራ አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደር እና የተገልጋይ እርካታ የዳሰሳ ጥናት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በብዙ ለውጥ የታየበት መሆኑ አበረታች መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ኢንስቲትዩቱ በያዝነው በጀት ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ የገባው ISO 21001_2018 አፈጻጸምን በተመለከተ በአቶ ሀማሴን ሀድገንበስ አቅርበዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/