ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 12ኛውን የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት እና 4ኛው ሀገር አቀፍ ክህሎት ውድድር “ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ቃል አከበረ
ቱ.ማ.ኢ ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም. አንጋፋው ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት 12ኛውን የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት እና 4ኛው ሀገር አቀፍ ክህሎት ውድድር በሰልጣኞች ምግብ ዝግጅት ፣ በመስተንግዶ፣ በተግባራዊ ምርምር ውድድሮች ፣ በስራ ቅጥር አውደርዕይ እና በደም ልገሳ መርሐግብሮች አከበረ። የክህሎት ውድድር ሳምንት ኢትዮጵያን ሊያስጠሩ የሚችሉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማውጣት እድል የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሞን ሶካ ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸው መሰል ስራዎች እንዲጠናከሩ አሳስበዋል ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው የክህሎት ውድድርና የእንግዳ ተቀባይነት ሳምንት ሰልጣኞች ራሳቸውን የሚፈትሹበት እንዲሁም አሸናፊ የሚሆኑበት ፣ተቋሙም ራሱን የሚያስተዋውቅበት የጥናትና ምርምር ውጤቶችን የሚያሳይበት ትልቅ ተቋማዊ በዓል ነው ብለዋል።
በመርሐግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የግሉ ዘርፍ አመራሮች፣ የማህበራት ቦርድ አባላትና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝቷል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et