“ከአንድ ጎበዝ ወንድ ጀርባ ወደፊት የምትመራ አንድ ጠንካራ ሴት አለች”

ብጡል የሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ድርጅት ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር 4ኛውን የእናቶች ምስጋና ቀን አክብሯል፡፡
የምስጋና መርሐግብሩ መሰራች የብጡል ሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ድርጅት ባለቤት ወ/ሮ ሰንዱ ጌታቸው የፕሮግራሙ ዓላማ እናቶች ላደርጉት አስተዋጽኦ ማመስገን መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሀንስ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖች አባቶች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እንደተናገሩት እናቶች በጀግነት ተጋድሏቸው ሀገርን አቅንቷል፣ ከአንድ ጎበዝ ወንድ ጀርባ ወደፊት የምትመራ አንድ ጠንካራ ሴት አለች በማለት የሴቶችን ሚና ገልፀዋል።
ሴቶች ከእናትነት ባለፈ በጀግንነት ፣ በሀገር ግንባታ፣ በአስተዳደር፣ በፈጠራ እና በሁሉም መስክ ያላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በምሳሌነት ተነስቷል፤ እናቶች ተመሰግነዋል፣በተለያዩ መስኮች ውጤታማ እና ምሳሌ ለሚሆኑ እናቶች እውቅናና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።
ይህ እናቶችን የማመስገን መርሀ ግብር ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/