ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደብረብርሃን ብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ በአሰልጣኞች አቅም ግንባታ፣ በትብብር ስልጠና እና በጥናትና ምርምር ዘርፎች እንዲሁም በትብብር ስልጠና አብሮ ሊሰሩ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመግባቢያ ስምምነቱ እንደተናገሩት ደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በቅርብ ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው ፤ አሁን የተደረገው ስምምነት የበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፤ በሌሎች ሀገራት ያየናቸውና ቁጭት ፈጥረውብን የነበሩ ሥራዎችን ቱሪዝም የሀገር እድገትን ለመደገፍ በሚያስችል መልኩ እንጠቀምበታለን ብለዋል፡፡
የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ የመግባቢያ ስምምነቱ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ የሰለጠነ የሰውሃይልን ወደገበያ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው በዘርፉ ጥናትና ምርምር ስልጠና እንዲሁም ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ለመስጠት በትብብር መስራቱ በብዙ መልኩ ተመራጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ከአደስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኝ መሆኑ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የሚያስተምር መሆኑ እንዲሁም በሀገራችን የቱሪዝም መስመር ታሪካዊና ሀይማኖታዊ የሆኑ የቱሪስት መስህቦች የሚገኙበት በመሆኑ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅንጅት መስራቱ በዘርፉ ራሳቸውን ለማሳደግ ላላቸው ሙያተኞች የተሻለ እድል አለው ተብሏል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et