በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞች ይሰጥ የነበረው የውጭ ሀገር ሥራ ስሚሪት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ
በEASTRIP ፕሮጀክት ድጋፍ ከተለያዩ ክልል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ለተወጣጡ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለሚሰጡ ለሦስተኛ ዙር እየተሰጠ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢንስቲትዩቱ የሥልጠና እና የተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ አቶ ተመስገን በቀለ እንደገለጹት ስልጠናውን ያገኙ አሰልጣኞች ወደ ተቋማቸው ስመለሱ እንደሀገር የተጣለውን ሀላፊነት እንዲወጡ አሳስበው የስልጠናውን ውጤታማነት አፈጻጸም ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
ስለ ስልጠናው አስተያየት የሰጡ ተሳታፊዎች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ስራ መቀጠር የሚፈልጉ ዜጎችን በሚገባ ለማሰልጠን እንዲያስችል የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና እድል በማመቻቸቱ እና ለአሰልጣኞችም ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አስተያየት የሰጡት የስልጠናው ተሳታፊዎች እንደሀገር ወጥ የሆነ ስልጠና ለመስጠት በሁሉም ማሰልጠኛ ማዕከላት ያለው የግብዓት አቅርቦት ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸው ችግሮችን ለመፍታት እንዲያስችል ለተቋማቱ አመራሮች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር ስልጠና ነው፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments