ኢንስቲትዩቱ አዲስ የሰልጣኞች መማክርት አቋቋመ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ እንዲቻል የሰልጣኞች መማክርት አቋቋመ።
የኢንስቲትዩቱ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ኢንስቲትዩቱ በክህሎት ፣ ሥነምግባር እና ዕውቀት ሰልጣኞቹን የሚያንጽ በመሆኑ ይህን በሚገባ ለመወጣት፤ የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ የሰልጣኞች መማክርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ስልጠናውን ስትከታተሉም ሆነ በትበበር ስልጠና በምትሰማሩበት ቦታ ተቋማችሁን ከፍ የሚያደርግ ተግባር ላይ እንድትገኙ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ የሰልጣኞች መብትና ግዴታን በሚመለከት ስልጠና የሰጡት የስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አስቻለው አደራ ስልጠናው እየተካሄደ ያሉ የጥራት መለኪያ መስፈርቶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ የተሻለ የስልጠና ሂደት እንዲኖር እንዲሁም ከስልጠና በኋላም ያሉ ክፈተቶችን መለየት ከሰልጣኞች ይጠበቃል ብለዋል። አሰልጣኞችም ዝግጅት በማድረግ፣ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና መስጠት ይገባቸዋል ብለዋል።
የቮኬሽናል ጋይዳንስ ፣ ካውንስልንግ አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ በበኩላቸው የሰልጣኞች ካውንስል መቋቋሙ በተለይ በትብብር ስልጠና ላይ ተገቢውን ክትትል ለማድረግ እና ሰልጣኞች ጋር ተደራሽ ለመሆን ያግዛል ብለዋል።
በሰልጣኞች ሥነምግባር መመሪያ፣ የሴቶች እኩልነትና ትንኮሳ መከላከል እና የስልጠና ጥራትን በሚመለከት አጠቃላይ መረጃ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም አስር ቋሚ እና ሶስት ተጠባባቂ አባላት ያሉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች መማክርት ተመርጠው የሥራ አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments