አዲስ የተዘጋጀው የዲግሪ ስርዓተ ትምህርት ዘርፉን መምራት የሚችል ባለሙያ ለማፍራት እንደሚረዳ ተገለጸ፡፡

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን ስልጠና ደረጃ ከፍ ለማድረግ የተዘጋጀው የሆቴል ማኔጅመንትና የቱሪዝም ማኔጅመንት ዲግሪ መርሀ ግብር ስርዓተ ትምህርት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተገምግሟል፡፡
የተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ዘርፉን በተግባርና በንድፈ ሃሳብ ከፍ ባለ ደረጃ መምራት የሚችል ባለሙያ ለማፍራት እንደሚያስችል የሁለቱንም ካሪኩለም ዝግጅት ያስተባበሩት ዶክተር ቢያድግልኝ አደመ ስለ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ባስረዱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
የቱሪዝም ሥርዓተ ትምህርት ያቀረቡት ኢንስትራከተር ተፈሪ አቡሀይ በበኩላቸው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ካለው የብዙ ዓመት ልምድ አንጻር ሲታይ አዲስ የተዘጋጀው ካሪኩለም በንድፈ ሃሳብ መምራት የሚችል፣ በተግባር ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥ ሙያተኛን ለማፍራት፣ ፖሊሲ ማውጣትና ለመተቸት አቅም ያለውን ሰው ለኢንዱስትሪው ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል፡፡
የተዘጋጀው ካሪኩለም በዘርፉ ስልጠና ከሚሰጡ ሌሎች ተቋማት የሚለይበት በተግባርና ንድፈ ሃሳብ የሚሰጡ ስልጠናዎችን ያጠመረ መሆኑን የገለጹት የሆቴል ማኔጅመንት ካሪኩለም ያቀረቡ ኢንስትራከትር ያለው ዘለቀ ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የራሱን የዘርፉ ካሪኩለም በማዘጋጀት በደረጃ ስልጠና እየሰጠ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲግሪ መርሀ ግብር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እየሰጠ እንደነበር ልብ ይለዋል፡፡
ከተሳታፊዎችም በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ መካተት የሚገቡ ጉዳዮች ሃሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ