ኢንስቲትዩቱ ከአወሊያ ኮሌጅ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የስልጠና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የአረብኛ ቋንቋ ስልጠና ለመጀመር ከአወሊያ ኮሌጅ ጋር አብሮ ለመስራት የጋራ ስምምነት ተፈርሟል፡፡
የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ የስልጠና ፍላጎት ያለው ተቋም በመሆኑ ይህን ለማሳካት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የአረብኛ ቋንቋ ስልጠና መስጠት መጀመር የስልጠና ተደራሽነቱን የሚያሳድግና በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለዜጎች ሰፊ የሥራ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ከአወሊያ ኮሌጅ ጋር በስልጠና፣ በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ በጥናትና ምርምር፣ በመምህራን ልምድ ልውውጥና በሥራ እድል ፈጠራ ዙሪያ አብሮ ለመስራት ሲሆን የአረብኛ ቋንቋ ስልጠናው በረጅምና አጭር ጊዜ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ለመስጠት መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
የአወሊያ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አሊ ሁሴን አረብኛ ቋንቋ ዓለም ላይ ብዙ ሀገራት የሚጠቀሙት በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ ጋር በስልጠናና ሌሎችም በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን፣ አብረን በመስራታችንም ደስይለናል ብለዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይረቴክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አሊ ሁሴን የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ፈርመዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ