ከወረዳ 11 ለተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጣቸው
የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ለማስፋት በቂርቆስ ክ/ከተማ ከወረዳ 11 ለተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናውን አስመልክቶ በተቋሙ የጥናትና ምርምር ክፍል ባለሙያ አቶ ሄኖክ መሐሪ እንደተናገሩት ከወረዳ 11 ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ምንነትና ዘርፉ የሚያስገኘውን የሥራ እድል አስመልክቶ በተለያዩ አሰልጣኞች ሰልጠና ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አሰልጣኞች አቶ ሰይድ ተስፋዬ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ ፣ አቶ ሀብቱ ተካ በቤት አያያዝና እንግዳ አቀባበል አቶ በቀለ ኡማ በቱሪዝም ዘርፍ የሚገኙ የሥራ ዕድሎችን የአንድ ቀን ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡
ማሰልጠኛ ኢንሰቲትዩቱ ከተሰጡት ተልእኮዎች አንዱ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጠት ሲሆን እስካሁን በተለያዩ አገልግሎቶች የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል ።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
Recent Comments