ሰልጣኞች ከትምህርት ባለፈ የቢዝነስ ሃሳብ የሚያዳብሩበት እገዛ እየተደረገ ነው
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሰልጣኞች በክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል (Incubation Center) ከስልጠና ባለፈ የቢዝነስ ሃሳቦችን የሚያዳብሩበት፣ ስራ ፈጣሪነትን የሚለማመዱበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ስልጠና ላይ የሚገኙት በማደራጀት በተቋሙ ያላቸውን የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ወደፊት መድረስ የሚፈልጉበትን እንዲለዩ፣ ተደራጅተው የቢዝነስ ሃሳባቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በዘርፉ ላይ ረጅም ዓመት ልምድ ባለቸው ሥራ ፈጣሪዎችና ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሰልጣኞቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ይታሰብ ሥዩም በፋይናስም ድጋፍ የሚያገበትንም ሁኔታዎች ለማመቻቸት እየተሰራ ነው፣ ከኢንስቲትዩቱ የሚወጡ ሰልጣኞች ተቀጣሪ ብቻ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ በመሆን ለሌሎች የስራ እድል የሚፈጥሩ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም ስለ ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል (Incubation Center) ዓላማና ከሰልጣኞች ስለሚጠበቁ ጉዳዮች፣ የቢዝነስ ሃሳብ ዕቅድ ዝግጅት እና የህይወት ክህሎት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ በኢንተርፕራይዝና ኢንኩቤሽን ማዕከል አስተባባሪ በአቶ መለሰ ወርቁ እና ሼፍ ፍሰሃ ሲሳይ ያላቸውን የካበተ ልምድ ለሰልጣኞች አካፍለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments